ብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ለልጆች ጥቅም ይሰራል፡፡
መረጃ ለወላጆች
ማህበራዊ አገልግሎቶች በልጆች ጥቅም ላይ ይሰራሉ, ብሮሹር
ብዙ ቤተሰቦች ከብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ እርዳታ ያገኛሉ
የብሄራዊ የጤና እና ደሕንነት ቦርድ በሁሉም ከፍለ ከተሞች ይገኛል፡፡ በዚያም ስለልጆች ፍላጎት የመጠቀ እውቀት ያላቸው የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኞች፤ ሁሉም ልጆች በደህንነት እና በጥበቃ ዉስጥ ማደግ የሚችሉበት ዕድል እንዲኖር ይሰራሉ፡፡ በተግባር ሲታይ፤ ከወላጆች አንዱ በስነልቦናው ድህነት የሚሰማው ወይም በማንኛውም የጥቃት ችግር ዉስጥ ያለን ቤተሰብ መርዳት ማለት ነው፡ ፡ ብሄራዊ የጤና እና ደሕንነት ቦርድ ለጥቃት የተዳረጉ እና የተጎሳቆሉ ልጆችን እና ወላጆችንም ጭምር ማገዝ አለበት፡፡
በመጀመሪያ ነገሮች በቤት ዉስጥ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሠራት አለባቸው
ብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ በብዙ መልኩ ሊረዳ ይችላል፡፡ ይህ የተለመደ ነው የትኛው አይነት እገዛ የበለጠ ተገቢ እንደሆነ ተስማምተናል፡፡ ጠና ያለ ግጭት የሚያጋጥማቸው ቤተሰቦች ለምሳሌ፤ ቤተሰቦች እነዚህን ችግሮች እንዲፈቱ በደንብ መርዳት የሚችል አንድ ሰውን ያግኙ፡፡ እንደ ወላጅ፤ በግል ወይይት ወይም በጋራ በሚደረግ ዉይይት እንደወላጅ ስላሎት ሚና እርዳታ ማግኘት ይቻላል፡፡ ለልጆች፤ መኖር የሚኖረው አገናኝ ሰው ማግኘት የሚቻልበት መንገድ ወይም ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙትን ልጆችን የማግኘት ዕድል ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ሁሉ ሰው ለእገዛ እና ለጥበቃ ማመልከት ይችላል
እገዛ እና ጥበቃ እንደሚያስፈልጎት የሚያስቡ ከሆነ የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድን ያግኙ እና ያሉበትን ሁኔታ ይግለፁ፡፡ አርዳታ እና እገዛ ለማግኘት ልጆችም ሆነ ወላጆች የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድን ለማነጋገር በእርስዎ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን ቢሮአቸውን ያግኙ። በክፍለከተማው ድህረ ገፅ፤ የስልክ ቁጥሮች እና ሌሎች የማግኛ መንገዶች መኖር አለባቸው፡፡
ስጋት ወይም ጭንቀት የሚሰማው ማንኛዉም ሰው በብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ጋር መሄድ መመዝገብ ይችላል፡፡
አንድ ልጅ በመጥፎ ሁኔታ እንደተያዘ የጠረጠረ ማንኛዉም ሰው ለብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ማሳወቅ ይችላል፡፡ ማሳወቅ እንዲህ ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ ለወላጅ ማሳወቅ አይደለም፤ ነገር ግን ስለሚያሳስብዎት ነገር ለልጅ ማሳወቅ ነው፡፡ ሰራተኞች በመዋለ ህፃናት፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም በጤና እንክብካቤ አገልግሎት፤ አንድ ልጅ በመጥፎ ሁኔታ እንደተያዘ ከጠረጠሩ፤ የግድ በህጉ መሰረት፤ ስለሚሳስባቸው ነገር ለብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
ሪፖርት የሚደረገው በቀጥታ ለብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ነው፡፡ አንድ ልጅ ስላለበት ሁኔታ ብቻ ለመጠየቅ ከፈለጉ፤ የልጁን ስም ሳይናገሩ ይህንኑ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ምን ይሆናል?
የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ አንድ ልጅ ጥበቃ እና እገዛ እንደሚያስፈልገው ካረጋገጠ፤
ለልጁ እና ለቤተሰቦቹ የሚጠቅመዉን የማወቅ ኃላፊነቱ የእነርሱ ሥራ ነው፡፡ ይህ ሂደት ልጁ
ያለበትን ሁኔታ መመርመር ተብሎ ነው፡፡ ወላጆችም ሆኑ ልጁም በምርመራዉ መሳተፍ እና
የበኩላቸውን ማድረግ አለባቸው፡፡ የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ በተጨማሪ ሌሎች ልጁን
የሚያዉቁ ለምሳሌ እንደ ዘመዶች እና አስተማሪዎችን ማነጋገር ይፈልጋል፡፡
የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ምን ይናገራል?
ከብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ጋር ግንኙነት የሚፈጥር ሰው ሁሉ ጥንቃቄ
የሚያስፈልጋቸው መረጃዎች ለሌላ እንደማይተላለፍ ማመን አለበት፡፡ የብሄራዊ የጤና እና
የደሕንነት ቦርድ መረጃዎችን የመጠበቅ ወሳኝ ኃላፊነት አለበት፤ ይህም ሚስጥር ጠባቂነት ይባላል፡
፡ እንደ አሳዳጊ፤ ልጅዎትን የሚመለከት ማንኛዉንም ነገር እንዲያዉቁ ይፈቀዳል፡፡ ነገር ግን
የብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ ልጁ ላይ ከባድ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል ነገርን አይናገርም፡፡
የልጁ እድሜ በጨመረ ቁጥር፤ የመወሰን መብቱም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ትላልቅ ልጆች አሳዳጊው
አንዳንድ መረጃዎችን እንዲያገኝ ፈቃድ እንዲሰጠው ማጽደቅ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡
ልጁ ከዚህ በኃላ በቤቱ የማይኖር ከሆነ የሚሰጠው እርዳታ
ከዚህ በኃላ በቤት ውስጥ መኖር ለልጁ የማይመች ከሆነ፤ ልጁ ለተወሰነ ጊዜ በሌላ ቦታ መኖር
ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ልጁ፤ ከሌላ ቤተሰብ( የቤተሰብ ቤት) ወይም በእንክብካቤ
መስጫ ቤት ውስጥ ወይም በመኖሪያ ቤት (HVB) ሊኖር ይችላል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ፤
ወላጆች ከብሄራዊ የጤና እና የደሕንነት ቦርድ እገዛ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ለምሳሌ፤ አንድ
ሰው የልጅ አስተዳደግ ችሎታዎችን በማሳደግ ላይ እርዳታ ማግኘት ይችላል፡፡ ዓላማው ሁልጊዜ ለ
ነገሮችን ለልጁ ጥሩ ማድረግ እስከሚቻል ድረስ ማድረግ ነው፡፡